• Home
LAURENDEAU & ASSOCIATES
  • Home

Startup Ecosystem Building: Insights from Japan

8/31/2021

1 Comment

 
Based on Bernard Laurendeau's Conversation with Nahoko Toyota - GM at Innovation Dojo Japan, GM at Kobe Global Mentorship Program and Startup Hub 
 
After the lost decade of the 1990’s in Japan, the number of temporary workers dramatically increased due to the economic stagnation. The shift in the labor workforce, which was historically dominated by large corporations, led to a change in mindset. In the late 2000’s, a startup ecosystem started emerging in Japan.
How has the mindset or startup culture evolved since then? Is the ecosystem growing? What proactive measures were taken to build the ecosystem? How are entrepreneurs fundraising? What does talent availability look like in this nascent ecosystem? We examine all these questions in our conversation with Nahoko Toyota.
 
A Timid Startup Culture

In general, the Japanese society is risk averse. However, when really looking hard at facts "in Japan the risk mainly exists in our minds" says Nahoko, “the worst thing that can happen for a young entrepreneur is for the startup to fail but there is always a social security system and companies hire candidates with entrepreneurial skills” she adds. Indeed, their livelihood or whole career success is not at stake, unlike in some developing countries. 
The Japanese society has traditionally been based on equality and uniformity; people still tend to hesitate to 'stand out'. Many top university students envision and aspire for a career in the government, as public servants, or working for large conglomerates also known as Zaibatsu’s, almost never for a small startup or as an entrepreneur.
This limited aspiration to work for startups is not a surprise because startups receive limited attention in the media and entertainment and "when you cannot see it, you cannot be it" according to Nahoko. However, there seems to be a shift in career aspirations in the last decade or so.
Increasingly, large companies have a Corporate Venture Capital (CVC) arm- usually structured as a separate entity- and intrapreneurship is encouraged. Many individuals who have gained experience in startup ecosystems abroad are integrated in large companies or startups in Japan and playing the role of 'interpreter' or 'intermediary', translating novel and disruptive approaches into the existing corporate or governmental environment, including highly regulated industries.
 
Startup funding

Access to finance has greatly improved and is less of an issue for growing startups in Japan. 
  • Seed/Early stage: Entrepreneurs have access to support programs and grants run by local governments.
  • Middle/Later stage: Entrepreneurs have access to VC capital (homegrown firms and from other countries) and CVC
  • Growth/Scale stage: Entrepreneurs have access to VC and CVC.
 
In addition, in the early stages entrepreneurs have access to Government led incubators and accelerators managed by private firms (e.g., Deloitte[1], 500Startups[2]) and staffed with individuals with experience in the private sector. For example, 'Innovation Officers' in Kobe city are contract-based public servants with experience working in the private sector.
 
Startup Regulatory Environment

Japanese startup entrepreneurs tend not to challenge the current laws and regulations but to find a way to co-exist with them while creating a better user experience.
The policies and regulatory environment leave whitespaces for entrepreneurship and innovation. Disruption in the Japanese startup ecosystem can be qualified as "harmonious" as there is a close linkage or symbiosis between the industry and the startup ecosystem (e.g. Docomo Ventures[3]). Incentives and interests are aligned between startupers, corporations, and policy makers which usually leads to little friction between all those ecosystem actors.
In addition, CxO's from scaling startups are starting to serve the ecosystem as angel investors and mentors for the next generation of startupers. Clusters are also formed to build innovation ecosystems like the Kansai (Kyoto-Osaka-Kobe) Startup Ecosystem[4].
 
Finding talent

Local talent is increasingly aware of the startup industry and interested in joining it although this has not become mainstream yet. There have been nationwide campaigns like J-Startup[5] to entice the youth to join the ecosystem and grow globally. Interestingly, a popular TV show from South Korea called startup[6] seems to have captured the attention of the youth and is democratizing the concept of startups as well.
Furthermore, attracting talent from abroad remains an option through the startup visa coordinated by the Ministry of Economy, Trade, and Industry (METI)[7] but coordinated at the municipality or city level. 
 
Taking stock

The Startup ecosystem in Japan is growing in its volume and breadth of disruption; “It is also developing its own uniqueness in comparison with over ten years ago when people were looking at Silicon Valley and pondering how to copy and paste it” says Nahoko.
Global standards and best practices have been incorporated into the startup ecosystem. According to Nahoko, “now that we learned what needs to be localized in the local context, I believe we are in a much better place to start, support, and invest in startups in Japan.”
 



[1] Tokyo Acceleration Program, Operating the Aoyama Startup Acceleration Center supported by the Tokyo Metropolitan Government, Deloitte, September 15, 2015

[2] 500 Startups Kobe Accelerator 500kobe.com & ecosystems.500.co/accelerate_aichi/growth_program

[3] NTT DOCOMO Ventures, https://www.nttdocomo-v.com/en/

[4] Turning the Kyoto-Osaka-Kobe Bay Area into a Global Startup Ecosystem, Jetro, May 25, 2021

[5] https://www.j-startup.go.jp/en/

[6] https://asianwiki.com/Start-Up_(Korean_Drama)

[7] https://www.meti.go.jp/english/policy/economy/startup_nbp/startup_visa.html
1 Comment

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እድሎች

8/2/2021

0 Comments

 
AUTHOR: Feven Dagnachew (Senior Manager, Laurendeau & Associates)


​መግቢያ

ኢትዮጵያ በፈጣን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦች ላይ እንደመገኘቷ ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለዓለም እያበረከተ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅዖ እየተመለከቱ በዝምታ ማለፍ አዋጭ አይሆንም ፡፡ ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ስለ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አስፈላጊነት የሚያስሱ ብሔራዊ ፖሊሲዎች ቢኖሩም አብዛኛዎቹ ለዋናው ስራ ሂደት (core business) ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ አስቻይ ለሆኑት መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ ነበሩ፡፡
ዲጂታል ትራንሰፎርሜሽን ማለት አሰራርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማገዝ መቻል ሲሆን አሠራርን ከማዘመነን በዘለለ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ መሆኑ ለፈጣን እድገት ምቹ ያደርገዋል:: በመሆኑም እ.ኤ.አ ከ2020 እስከ 2024 ዓ.ም በአጠቃላይ 7.8ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። [1]
 
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ 2020 እስከ 2025

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ እያረገ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተለያዩ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ መሳሪያዎችን እያስተዋወቀ እና ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ ከነዚህም ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መካከል እ.ኤ.አ. ከ 2020 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረገው  ብሄራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ አንዱ ነው፡፡ ይህም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ በአገሪቱ አስተማማኝ እና ውጤታማ አዳዲስ የስራ እድሎች መፍጠር ፣ ድህነትን ለመቅረፍ የሚችል እድገትን ለማስፋፋት እና አዳዲስ ዲጂታል ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም የመወዳደር አቅምን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡
ስትራቴጂው ከብሄራዊ ሶሺዮኢኮኖሚክ እና እድገት እቅዶች ከሆኑት ከብሄራዊ የ10 ዓመት የልማት እቅድና እና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ በተመሳሰይ ሁኔታ ስትራቴጂው ከአህጉሩ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እና ከተባበሩት መንግስታት ከዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሁም ከተለያዩ የአለም አቀፍ ኢኒሼቲቮች ጋር የተጣጣመ ነው፡፡
 
ለፈጠራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መንግስት የወደፊቱ እና የመፃሂ በቴክኖሎጂዎች ምርምርና ስርፀት ላይ በቁርጠኝነት መዋለንዋይ ፈሰስ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
 
 
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭስ
 
አገሪቱ እየተጓዘችበት ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መንገድ በመከተል አዳዲስ ተነሳሽነቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ኢኒሼቲቮች መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው ላለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት በመንግስት ተይዞ የነበረውን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነፃ ማድረግ ነው፡፡ የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉን ነፃ ማድረግ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ዕድሎች እና ጠቀሜታዎች ይሰጣል፡፡ ከነዚህም መካከል ተወዳዳሪ እና ጥራት ያለው የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ከመስጠት ባሻገር በማደግ ላይ ባለው የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ውስጥ ልምዱ እና አቅሙ ያላቸው ዓለም አቀፍ ኦፕሬተሮች ተሳትፎ የሞባይል ባንክ አገልግሎት ለማስፋፋትና ለማጠናከር እንዲሁም አገሪቱ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የምታደርገውን ጉዞ ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ መጀመር፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም፣ የዲጂታል ክህሎት ሀገራዊ የድርጊት መርሃ ግብር፣ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ እና ሌሎች በመንግስት እየተወሰዱ ከሚገኙ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እንቅስቃሴዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ [2]
 
ተጓዳኝ እድሎች
​

አገልግሎት ሰጪ የሆኑ የመንግስት ተቋማት አሰራራቸውን ዲጂታላይዝ በማድረግ እና ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመንግስት (e-government) አሰራር ስርዓት ተግባራዊ በማድረጋቸው በወረቀት ላይ የተመሰረቱ የስራ ፍሰቶች ወደ ዲጂታል ማህደሮች መቀየር ፣ አገልግሎቶች በተጨማሪ በበይነመረብ መድረኮች መስጠት የሚችሉበትን አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡ ይህም የሀገር ውስጥ የሶፍትዌር ልማት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ የኢንኩቤሽን ማዕከላት፣ የስታርት አፕ ፐሮግራሞች፣ የስታርት ሃፕ ፈንዶች እና የኢኖቬሽን ከባቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ እና እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡ [3]
 
የዲጂታል ክፍያው የኢ-ኮሜርስ ዘርፉን በሀገር አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ እና በማስፋፋት ረገድ የማይተካ ሚና ይኖረዋል፡፡ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው እንደ ግብርና እና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡
 
እነዚህን ሁሉ የዲጂታል ለውጦች ተከትሎ የድርጅት ሃርድዌር፣ ሶፍትዌሮች እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም ለአከባቢው ደንቦች እና ለደንበኛ ባህሪ የሚስማሙ መፍትሄዎች ፍላጎት ይጨምራል፡፡ ዲጂታል ኢኮኖሚው የመረጃ ማከማቻ እና የመከላከያ መገልገያዎች ወይም መሰረተ ልማቶች፣ ንግድ ለንግድ (B2B) መፍትሄዎችን ፣ የጥራት ማረጋገጫ ስርዓቶችን ወዘተ ይፈልጋል፡፡
 
 
ምክረ ሀሳባች

  1.   በጀት መመደብ፡ እ.ኤ.አ. ሰኔ 5 ቀን 2021 የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሀገሪቷ ታሪክ ከፍተኛ የሆነው የ2014 በጀት ዓመት ጠቅላላ በጀት 562 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አፅድቋል፡፡ ነገር ግን ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በቀጥታ የተመደበ ገንዘብ ግን የለም፡፡ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ለማሳካት አስፈላጊ የሆነ በጀት በአገር ደረጃ መመደብ ያስፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እያንዳንዱ ተቋም ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ተግባራት የበጀት መስመር ወይም መደብ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህ ለዲጂታል ለውጥ በውጭ ድጋፍ ላይ መተማመንን መቀነስ ያረጋግጣል፡፡
  2. የግዢ ስርዓትን ማሻሻል፡ አሁን ያሉት የግዥ ስርዓት መንግስት ለመንግስት(G2G) እንዲሁም በመንግስት እና በንግድ ተቋማት (G2B) መካከል ያለውን ግብይት እያሽመደመደ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ተለዋዋጭ፣ ውጤታማ እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን  ከግል ሴክተሮች ለማግኘት የግዢ ስርዓቱ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል፡፡የተማከለ አሰራር፡ በትላልቅ ብሔራዊ ፕሮግራሞች ላይ ብሔራዊ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከር ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ውጤታማ የሆነ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲኖር አሰራርን የተማከለ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ቴክሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት (TechIN) ትላልቅ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሞችን በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን የተሰጠው ተቋም ሲሆን የፕሮጀክቶችን አስፈላጊነት በማረጋገጥ እና ተገቢውን የመተግበሪያ ስነ ዘዴ በመቅረፅ የማስፈፀም ጥሩ አቋም ላይ ይገኛል፡፡ ወደፊት ተቋሙ የበለጠ ማበረታታት ይገባል ፡፡
  3.  መልካም ተሞክሮዎችን መቀመር እና ተግባራዊ ማድረግ፡ አሁን ባለው ሁኔታ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንነ እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ የተለመዱ የእድገት ደረጃዎችን መከተል አያስፈልጋትም። ኢትዮጵያ በተፈተኑ እና በክፍል ውስጥ የተሻሉ መፍትሄዎችን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን በሂደት እና በፕሮጀክት አስተዳደር ዘዴዎች እንኳን በጥንቃቄ መዝለል (leapfrog) ትችላለች ፡፡
  4.  ብቁ እና ውጤታማ አመራር፡ ለአፈፃፀም ስኬት  አመራር ቁልፍ ድርሻ ይወስዳል፡፡ ዲጂታል ሴክተር ተሻጋሪ (cross cutting) ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን መጠነ ሰፊ የሆነ ትብብርን በባለድርሻ አካላት መካከል ይጠይቃል፡፡  በተለይም በ ኢ-መታወቂያ (eID), ኢ-ሎጂስቲክ(eLogistics), ብሄራዊ የጊግስ መድረክ (National Gigs Platform), ዲጂታል ማፒንግ (Digital Mapping), ቱሪዝም, ዲጂታል ግብይት (Digital Marketing), ወዘተ ውጤታማ መሆን የሚያስችል ቀላጣፋ ውሳኔ እየሰጠ ለቴክኖሎጂ መፍትሔዎች  አዎንታዊ ምላሽ የሚያሳይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን (Czar) ሊኖር ይገባል፡፡ ለምሳሌ : እኤአ በ2009 ዓ.ም የአሜሪካው ኘሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሀገራቸው በሳይበር ሴኩሪቲ ጥቃት ላይ መሆኗን ሲገነዘቡ ጉዳዩን የሚመራ፣ የሚያስተባብርና የሚወስን ግለሰብ (cyber security czar) ሾመዋል። በተያያዘም ስራዉን በቀጣይነት ለመስራት እንዲያስችል የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀርፀው ስራውን በቅልጥፍናና ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚመራ chief technology officer (CTO) በመሾም ነፃ  የውሳኔ አሠጣጥ መዘርጋት ተችሏል።[4]
  5. ለውጥን ማስተዳደር፡ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሀሳብን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስረፅ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት እና በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ ተግባር ተከናውኗል፡፡ ነገር ግን በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነቱን እና ተፈፃሚነቱን ለማሳደግ በዘርፉ ውጤታማ በሆኑ አካላት የተለያዩ ስትራቴጂካዊ ዘመቻዎች ተቀርፀው ተግባራዊ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡


 
ማጣቀሻ
[1] Digital transformation spending worldwide 2017-2024, Kimberly Mlitz , Jul 28, 2021
[2] Home-grown Economic Reform Agenda Progress Highlight 2012EC, Federal Democratic Republic of Ethiopia - Ministry of Finance, June 2021
[3] Digital Ethiopia 2025: A Strategy for Ethiopia’s Inclusive Prosperity, Federal Democratic Republic of Ethiopia - Ministry of Innovation and Technology, June 2020
[4] Barack Obama to name a “Chief Technology Officer”, VentureBeat, Matt Marshall, November 13, 2007
0 Comments

    Archives

    May 2022
    March 2022
    September 2021
    August 2021
    July 2021
    June 2021
    May 2021
    April 2021

    RSS Feed

Copyright © 2023 Laurendeau & Associates
  • Home